ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የመንግስትን ገቢ ለማሳደግ ያለመውን የገቢ ግብር ንቅናቄ ዛሬ በይፋ አስጀመሩ፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ በሀገር አቀፍ የግብር ንቅናቄ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች

• ሰላም ግብርና የፍትህ ስርዓት ለአንድ አገር መሰረት ናቸው
• ያለጠንካራ የፍትህ ስርዓት ጠንካራ መንግስት መመስረት አይቻልም
• ፍትህና ሰላም እንደ እንቁላልና ዶሮ አንዱ አንዱን ተከትሎ የሚመጣ ነው
• መንግስት ሰላም እና ፍትህን ማስፈን የሚችለው ግብር መሰብሰብ ሲችል ነው፡፡ ያለዚያ ሽባ መንግሰት ይሆናል፡፡
• የበለጸጉ አገራት ታሪክ የሚያሳየው ሀገራዊ አቅም የሚገናባው ከህዝብ የሚሰበሰብ ግብር ነው፡፡ ግብር ለመንግስት እንደ ኦክስጅን ይቆጠራል፡፡
• ግብር ባለመክፈል ከሚደርሰው ኪሳራ ይልቅ በመክፈል የሚናገኘው ኩራት ይበልጣል፡፡
• ግብር የግል ዘርፉ ጠንካራና ተወዳዳሪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ለመሰረተ ልማት ማስፋፋያ ያስፈልጋል
• ያለመሰረተ ልማት ጠንካራና ተወዳዳሪ የግሉን ዘርፍ መፍጠር አይቻልም፡፡
• ግብር ማለት የሰለጠነ ማህበረሰብ እንደሰለጠነ ለመቆየት የሚከፍለው ዋጋ መሆኑን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡
• የግብር ታሪክ ከሰው ልጅ ስልጣኔ ጋር የሚቀራረብ ነው፡፡ ከሰው ልጅ ስልጣኔም የሚተሳሰር ነው፡፡ ለዚህም የስልጣኔው ምልክት ተደርጎ የሚወሰደው፡፡
• ኢትዮጵያችን የሰለጠነች እንዲትሆን ስለግብር ያለንን አስተሳሰብ መቀየር ያስፈልጋል፡፡ ግብር የማይከፍል እንደ አራዳ ሳይሆን እንዳልሰለጠነ ሊቆጠር ይገባል፡፡
• ኢትዮጵያ ከጠቅላላ ሀገሪዊ ገቢ 10. 7 በመቶ ብቻ በመክፈል ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ዝቅተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
• በሀሪቱ የተከሰቱ አለመረጋጋቶችም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖብናል፡፡
• ከማኪያቶ አንድ ዶላር በተባለው መርሃ ግብር ከ3 ሚሊዮን ዳያስፖረዎች 2 ሺ 800 ብቻ ናቸው እየተሳተፉ የሚገኙት፡፡
• ህገ-ወጥነት የግብር ስርዓታችን በካቴና አስረውታል፡፡ የዜጎችን ደም መጠዋል፡፡
• ያለፈውን ለመማር እንጂ የፊታችንን የተሻለ ለማድረግ መትጋት ያስፈልጋል፡፡
• እንደ መንግስት አጭበርባሪዎችን ብቻ ከመቅጣት በተጨማሪ በአግባቡ የሚከፍሉትን ማበረታት እንጀምራለን፡፡
• ግብር ከፋዩ ያለ እንግልት በተንቀሳቃሽ ስልክ ጭምር የሚከፈልበት መንገድ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡
• ግብር ከፋዩን የሚያንገላታ የመንግስት አካላት ከግብር አጭበርባሪው ጋር ተለይቶ ሊታይ አይገባም፡፡
• የተሳሳተ መስመር ውስጥ ያላችሁ ቀኑ ከመጨለሙ በፊት መደመር አለባችሁ

#EBC ኢቲቪ 4 ማዕዘን 6 ሰዓት አማርኛ ዜና በቀጥታ ይከታተሉ

Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Friday, 21 December 2018