ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአለም ኢኮኖሚ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአለም ኢኮኖሚ ጉባኤ (World Economic Forum) ፕሬዝዳንት ቦርገ ብሬንደን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ::
በውይይቱ ወቅትም ፕሬዝዳንቱ የአለም ኢኮኖሚ ጉባኤ (World Economic Forum) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚያደንቅ ገልፀው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በመጪው ጥር ወር 2011 ዓ.ም በዳቮስ ሲውዘርላንድ የሚካሄደው ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል::
ምንጭ፡ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት